የደም መርጋት በሽታ – ለታካሚዎች መረጃ

ሰላም ጤና ይስጥልኝ!
እኔ ዶ/ር ዳግም ለይኩን ፣ የደም ስር ቀዶ ሐኪም ነኝ:: በዚህ ጽሁፍ ስለ የደም መርጋት በሽታ እና ማድረግ ስላለብን አስፈላጊ  ነገር እንዳስሳለን::  ግን አይጨነቁ; ደም መላሽ ስሮችን እንዴት ከደም መርጋት እንደሚከላከሉ እና ጤናማ ማድረግ  እንደሚችሉ ለመምራት እዚህ ነኝ!

የደም መርጋት ምንድን ነው?

የደም መርጋት በደም ሥራችን ውስጥ ትንሽ መጓጎል ሲሆን ይህም ስንቆረጥ የደም መፍሰስን ለማስቆም ይረዳል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ትናንሽ መጓጎሎች በተለይም በእግራችን ጥልቅ ደም መላሽ ስሮች ላይ ችግር ሊፈጥሩ ይችላሉ። “Deep Vein Thrombosis” ወይም ባጭሩ “DVT” ብለን እንጠራዋለን ።

DVT ለምን አሳሳቢ ነው፡-

  1. የደም መርጋት እና ደም መላሾች መዘጋት በእግሮችዎ ውስጥ ባሉ የደም መላሽ መንገዶች ላይ የደም መመለስን መጨናነቅ ይፈጥራል። የደም መርጋት የደም መላሾች መዘጋት ሊያስከትል ይችላል, እብጠት እና ህመም ይፈጥራል::
  2. የረጋ ደም ወደ ሌላ ደም ስር መወተፍ፡- አንዳንድ ጊዜ እነዚህ የደም መርጋት ወደ ሌሎች የሰውነታችን ክፍሎች እንደ ሳንባ በመጓዝ የመተንፈስ ችግር ሊፈጥሩ ይችላሉ። ያ “የሳንባ ደም ስር መዘጋት” ወይም “Pulmonary Embolism” ይባላል.

DVTን ቀደም ብሎ ማወቅ፡-

  1. እብጠት እና ህመም፡- አንደኛው እግርዎ በድንገት ቢያብጥ ወይም ህመም ካለው ለእርስዎ እንደ ምልክት ነው። ወዲያውኑ ለሐኪምዎ ይንገሩ!
  2. ሙቀት እና መቅላት: ሙቀት ይሰማዎታል ወይም በእግርዎ ላይ መቅላት ይታይዎታል? ትኩረት እንዲሰጡ የሚነግር ምልክት ነው።

ሕክምናው፡-


ፀረ ደም መርጋት መድኃኒቶች፡- እነዚህ መድኃኒቶች የደም መጓገሎች እንዳይራቡ እና ወደ ሌላ ደም ስር እንዳይጓዙ የሚከላከሉ ጠቃሚ መድሃኒቶች ናቸው። እነሱ በመርፌ ወይም በክኒኖች መልክ ሊሰጡ ይችላሉ:: ህክምና የሚያስፈልግዎ ከሆነ፣ ሙሉ ለሙሉ ከደም መርጋት አደጋ ነፃ መሆንዎን ለማረጋገጥ ዶክተሮች በሆስፒታል ውስጥ ሆነው እንዲታከሙ ሊያደርጉ ይችላሉ።

የመከላከያ መንገዶች፡-

  1. መንቀሳቀስዎን ይቀጥሉ፡- ተነስተው በየሰዓቱ ወይም በየሁለት ሰዓቱ ይራመዱ፣በተለይ ረዥም በረራዎች ወይም የመኪና ጉዞዎች በሚያደርጉበት ጊዜ መንቀሳቀሶን እንዳይዘነጉ።
  2. በቂ ፈሳሽ ይውሰዱ እና ምቹ ልብሶችን ይልበሱ፡- ብዙ ውሃ ይጠጡ እና በእግር የደም ሥሮች የደም ምልሰት የተቀላጠፈ እንዲሆኑ ለማድረግ አመቺ ልብስ ይልበሱ።
  3. የመጭመቂያ ካልሲዎች፡- እነዚህ ለእግርዎ ጭን ድረስ የሚደርሱ ካልሲዎች  ናቸው፣ ሁሉም ደም መላሾች ያለችግር ደም እንዲመለስ ያደርጋሉ።
  4. በረዥም ጉዞ ጊዜ አልኮል እና ለእንቅልፍ የሚወስዱ መድሃኒቶችን ይዝለሉ። የመንቀሳቀስ አቅማችንን ሊያዘገዩ ይችላሉ።

አስታውሱ፣ ሰውነታችንን መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው! የእግር ደም ስራችንን ጤናማ እንዲሆን በማድረግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ ለማድረግ ዝግጁ መሆን እንችላለን!

መረጃውን ለጓደኞች እና ለሚወዱት ሰው ማጋራትዎን አይርሱ!

ዶ/ር ዳግም ለይኩን፣ የደም ስርዎ ደህንነት ላይ ታማኝ አጋርዎ።

እግሮቻችንን ጤናማ ማድረግ፡ የእግር ጋንግሪንን የመከላከል መመሪያ

  • ጤና ይስጥልኝ ፣ ዛሬ፣ ስለ አንድ ጠቃሚ ነገር እንነጋገር፡ እግሮቻችንን ጤናማ ማድረግ። እግሮቻችን ደም የሚሸከሙ ትናንሽ መንገዶች ደም ስሮች በውስጣቸው እንዳሉ ያውቃሉ? ደህና፣ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ መንገዶች “ጋንግሪን” የሚባል ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል። ግን አይጨነቁ፣ እንዴት መከላከል እንደምንችል ከዚህ ጽሁፍ ፍንጭ ያገኛሉ!

የእግር ጋንግሪን ምንድን ነው?


የእግር ጋንግሪን ማለት የእግራችን ክፍል ህብረ ህዋሶች  በቂ ደም ሳያገኙ ሲቀሩ እና መሞት ሲጀምሩ ነው። ይህ እግር ላይ ከሚደርስ ጉዳት፣ ከኢንፌክሽን ወይም ከሌሎች ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። የእግር ደም ስሮችን ጤናማ እና ብቁ ሆነው እንዲቆዩ ለማድረግ በርከት ያሉ ነገሮችን ማድረግ እንችላለን።

የእግር ጋንግሪን ለምን ይከሰታል: መንስኤዎች እና አደጋዎች


1.  ከባድ ጉዳቶች፡- ከባድ አደጋዎች አንዳንድ ጊዜ በእግራችን ላይ ባሉት የደም ስሮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።
2. የእግር የደም ስር በሽታ፡- የደም ስሮቻችንን እንደ ደም መንገዶች አስቡት። በጣም ጠባብ ከሆኑ ደም ወደ እግሮች የማድረስ ሁኔታን መጨናነቅን ሊያስከትል ይችላል!
3.  የስኳር በሽታ፡- የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች እግሮቻቸው ላይ ተጨማሪ ክትትል ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።
4.  የበሽታ መከላከል ስርዓት ተግዳሮቶች፡-  በሽታ የመከላከል ስርዓታችን በተለያዩ ሁኔታዎች የተዳከመ ከሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።
5.  ቀዶ ጥገና፡- አንዳንድ ጊዜ ቀዶ ህክምና በሚደረግበት ጊዜ የጋንግሪን ተጋላጭነት ይጨምራል።

የእግር ጋንግሪንን ቀደም ብሎ ማወቅ፡


1.  የቀለም ለውጦችን መኖራቸውን ያረጋግጡ፡ በእግር ላይ ያለው የቆዳችን ክፍል ወደ ሰማያዊ ወይም ጥቁር ከተለወጠ ዋነኛ ምልክት ነው – እርምጃ ለመውሰድ መፍጠን አስፈላጊ ነው!
2.  መጥፎ ሽታ ያለው ፈሳሽ፡ ቆዳችን ደስ በማይሰኝ መጥፎ ሽታ ያለው ፈሳሽ ያመጣ ከሆነ ለሚከተለው ሀኪም ማሳወቅ አለብን።
3.  የማያቋርጥ ህመም ወይም ትኩሳት፡-የማያቋርጥ ህመም ከተሰማን ወይም የማይጠፋ ትኩሳት ካለብን አንድ ነገር እንዳለ ሰውነታችን እያስጠነቀቀን ነው።


ከእግር ጋንግሪን መከላከያ መንገዶች


1.  ቁስሎችን ወዲያውኑ መታከም፡- ቆዳችን የተቆረጠ ወይም የተቧጨረ ከሆነ ወዲያው እናጽዳው እና የጤና ባለሙያዎችን እርዳታ እንጠይቅ።
2.  ለውጦችን ይከታተሉ፡ እንደ መቅላት፣ እብጠት ወይም ፈሳሽ ነገር ያሉ እንግዳ ነገር ካየን ለጤና ባለሙያዎች መንገር አለብን።
3.  መደበኛ ፍተሻዎች፡- በተለይም የስኳር በሽታ ወይም የደም ስር ችግር ካለብን መደበኛ ቼክአፕ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ያስታውሱ፣ የእግር ደም ስሮቻችን ቀደም ብለው መታከማቸው ጤናማ እንዲሆኑ እና የደም ፍሰት መጨናነቅን ለማስወገድ ይረዳናል። እንግዲያው፣ እግሮቻችንን ጤናማ እናድርግ፣ እናም ከጭንቀት ነፃ ሆነን እየሮጥን ህይወታችንን መምራት እንችላለን!

ዶ/ር ዳግም ለይኩን – የደም ሥር ቀዶ ጥገና ሐኪም በኢትዮጵያ

Empowering Vascular Surgery in Ethiopia: A Journey of Growth and Collaboration

Grateful for the Opportunity to Make a Difference in Vascular Surgery in Ethiopia!

As a vascular surgeon at Hawassa University, every day brings new challenges and rewarding milestones. Today, I’m excited to share a significant point in my journey—a successful completion of my second case of aortic aneurysm repair with a graft for a ruptured abdominal aortic aneurysm.

In my previous case, I faced complexities of the case because of lack of graft material, pushing me to improvise and utilize the patient’s femoral vein. Despite the challenges, this experience became a valuable lesson, laying the foundation for my growth in the field of vascular surgery.

Fast forward less than a month, and the opportunity to make a difference presented itself once again. This time, I had the privilege of utilizing graft material generously donated by compassionate individuals. Their generosity streamlined the operation, allowing me to reduce the procedure time by half.

Ruptured abdominal aortic aneurysm
Ruptured AAA Repair

The Impact of Collaboration in Vascular Surgery in Ethiopia

I am truly humbled by the support and resources that make these life-saving interventions possible. The donated graft used in this case is a testament to the collaborative spirit driving advancements in Vascular Surgery in Ethiopia.

This experience emphasizes the critical importance of recognizing and addressing challenges faced in Vascular Surgery, especially in Low- and Middle-Income Countries (LMICs). As a community, let’s champion the need for accessible and affordable supplies that significantly impact patient outcomes.

A Call to Action for Vascular Surgery in Ethiopia

I’m excited to share this journey and invite discussions on the evolving landscape of Vascular Surgery in Ethiopia and Hawassa University Hospital. Your insights and support are invaluable, and together, we can raise awareness about the importance of resources in achieving successful outcomes in this vital field of medicine.

Join me in spreading the word about Vascular Surgery in Ethiopia, and let’s continue saving lives and limbs together!

Dr. Dagim Leykun

Vascular Surgeon

Spider Veins

Spider veins
Spider Veins

የቫሪኮስ ቬይን መጭመቂያ ካልሲዎች (Compression Stockings) ቫሪኮስ ቬይንን ለማከም ይረዳሉ?

የቫሪኮስ ቬይን መጭመቂያ ካልሲዎች

ቫሪኮስ ቬይን ከቆዳው ወለል በታች የሚገኝ በጣም ጎልቶ የሚታይ የደም ስር ነው:: የመጭመቂያ ካልሲዎች የቫሪኮስ ቬይን ስሮቾን እይታ በመቀነስ እና በአንዳንድ ሰዎች ላይ ሕመሙን ለማስታገስ በመርዳት ሊያግዙ ይችላሉ::

የቫሪኮስ ቬይን ስሮች የሚከሰቱት ደም ከእግሮች ወደ ልብ በተቀላጠፈ ፍሰት መጓዝ ስለሚኖርባቸው ከመመለስ ይልቅ በእግሮች የደም መላሽ ስሮች ውስጥ በሚገኙ ትናንሽ ቫልቮች በስተጀርባ በሚሰበሰብበት ጊዜ ነው። የቫሪኮስ ቬይን በእግሮች ላይ በጣም የተለመዱ ችግሮች ናቸው።  ዶክተሮች ብዙውን ጊዜ የደም ዝውውርን ለማሻሻል፣ የ የቫሪኮስ ቬይን እንዳይባባሱ እና ህመምን ወይም ምቾት እንዳይቀንስ የመጭመቂያ ካልሲዎችን ይመክራሉ።

የመጭመቂያ ካልሲዎች የደም ዝውውርን ለማሻሻል እና የ የቫሪኮስ ቬይን ምልክቶችን ለማከም ሊረዱ ይችላሉ:: ዘመናዊ የመጭመቂያ ካልሲዎች በእግሮች ውስጥ ወጥነት ያለው ግፊት እንዲኖር ለማድረግ የተነደፉ ናቸው ደም ወደ ልብ እንዲመለስ ይረዳል ስለሆነም የበለጠ ተመራጭ ናቸው::  የመጭመቂያ ካልሲዎች ብዙውን ጊዜ በቁርጭምጭሚት እና በእግሮች አቅራቢያ የበለጠ ግፊት ይፈጥራሉ፣ ይህም የደም ፍሰትን የሚያበረታታ ተጨማሪ መጭመቅ ይሰጣል::

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የመጭመቂያ ካልሲዎች የ የቫሪኮስ ቬይን አንዳንድ ምልክቶችን ሊያሻሽሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን የመጭመቂያ ካልሲዎች ብቻውን የቫሪኮስ ቬይንን ያስወግዳቸዋል የሚለውን ሃሳብ የሚደግፉ ጥቂት ማስረጃዎች አሉ። ሆኖም የቫሪኮስ ቬይንን ለማስወገድ የቀዶ ጥገና ህክምና ከመጭመቂያ ካልሲዎች የበለጠ ውጤታማ ህክምና ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል።

የትኛውን ዓይነት የመጭመቂያ ካልሲ መጠቀም አለብኝ?

የተለያዩ ዓይነቶች የመጭመቂያ ካልሲዎች የተለያየ መጠን ያለው ግፊት ወይም መጭመቅ ያደርጋሉ:: ትክክለኛው የግፊት መጠን እና ትክክለኛው የአለባበስ ዓይነት በሰውዬው የቫሪኮስ ቬይንን ብዛት፣ ዓይነት እና መሰረታዊ ምክንያት ላይ የተመሰረተ ነው። ሦስቱ ዋና ዋና የመጭመቂያ ካልሲዎች ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው::

1. እንደ ሱሪ የሚጠለቅ:- እነዚህ የተወሰነ ግፊት ይፈጥራሉ፣ ግን የመጭመቅ ችሎቴቸው ከሌሎቹ ቀነስ ያሉ አማራጮች ናቸው።

2. የመጭመቂያ ካልሲዎች (ረጅም ወይም አጭር):– በብዙ የመድኃኒት ሱቆች እና በፋርማሲዎች ውስጥ ለመግዛት ይገኛሉ። እነዚህ እንደ ሱሪ ከሚጠለቅ አይነቶቹ የበለጠ መጭመቅ ይሰጣሉ።

3. በሐኪም የሚታዘዙ መጭመቂያ ካልሲዎች:– እነዚህ ከፍተኛውን መጭመቅ/ግፊት ይፈጥራሉ፣ ውጤታማ እንዲሆኑ በባለሙያ ትክክለኛው መጠን እና ቅርጽ የታዘዘ  መሆን አለበት ነገር ግን የደም ዝውውርን የሚነካ በጣም ጠባብ እንዲሆን አይፈለግም።

የመጭመቂያ ካልሲዎች በአብዛኛው ጉልበት ድረስ የሚደርሱ ወይም ከጉልበት ከፍ ያሉ ናቸው።  ከጉልበት ከፍ ያሉ የመጭመቂያ ካልሲዎች ብዙውን ጊዜ በሀኲሞች ይመከራሉ:: የባት ጡንቻዎች በእንቅስቃሴ ጊዜ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ጊዜ በታችኛው እግር ውስጥ የደም ዝውውርን ያበረታታሉ።

የመጭመቂያ ካልሲዎችን መቼ መልበስ አለብኝ?

የቫሪኮስ ቬይን ያለባቸው ሰዎች በቀን ተቀን እንቅስቃሴያቸው ውስጥ የመጭመቂያ ካልሲዎችን መልበስ ይኖርባቸዋል፣ ምክንያቱም ቀጥ ብሎ መቆም እና መቀመጥ የደም ዝውውር ላይ ችግሮች የመፍጠር ዕድላቸው ሰፊ ነው:: ቫሪኮስ ቬይን ያለበት ሰው የደም ዝውውሩን ለማሻሻል ሌሊት እግሮቹን ወደ ላይ ከፍ ማድረግ ይኖርበታል። በተጨማሪም በሌሊት የመጭመቂያ ካልሲዎችን እንዲለብሱ ሊመከር ይችላል።

የመጭመቂያ ካልሲዎች ሲያደርጉ ማድረግ ያለብዎት ጥንቃቄ

የመጭመቂያ ካልሲዎች በተሳሳተ መንገድ ወይም ለረጅም ጊዜ ከተለበሱ አደጋዎች አሏቸው የቆዳ መቆጣት ሊያስከትሉ ይችላሉ።  የመጭመቂያ ካልሲዎች ሆን ብለው ጠባብ ስለሆኑ ለመልበስ አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ:: እግሮቹ ንጹሕ እና ደረቅ መሆን አለባቸው። ካልሲዎችን ከመልበስዎ በፊት ማንኛውም ሎሽን በማድረግ ቆዳውን ያለስልሱ።

የመጭመቂያ ካልሲዎችን መጠቀም የሚከተሉትን ጨምሮ የጐንዮሽ ጉዳቶች ሊኖረው ይችላል:: የቆዳ መሰንጠቅ፣ የቆዳ መቆጣት፣ ምቾት ማጣት፣ ቆዳ ላይ ጊዜያዊ ህመም ወይም የመጨመቅ ምልክት ናቸው::

የተበጣጠሱ ካልሲዎች፣ በተሳሳተ መንገድ የተለበሱ ወይም የተሳሳተ መጠን ያላቸው ካልሲዎች ችግር የመፍጠር ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። በተለይ እንደ ነርቭ  እና የደም ዝውውር ችግሮች የለባቸው ሰዎች ነርቮችን ወይም የደም ዝውውርን ሊጐዳ የሚችል ሁኔታ ሊያስከትሉ ይችላል::  ይህም ካልሲዎቹ በጣም ጠባብ ስለሆኑ ወይም ወደ ታች እየወደቁ በመሆኑ ሊሆን ይችላል።

አንድ ሰው የመጭመቂያ ካልሲዎችን ለረጅም ጊዜ የሚለብስ ከሆነ አሉታዊ ተጽዕኖዎች የመጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ስለዚህ የመጭመቂያ ካልሲዎችን በየቀኑ አውልቀው እግሮችን የጉዳት ወይም የእብጠት ምልክቶች ይፈትሹ። ጥሩ ውጤቶችን ለማግኘት እግሮቹን እና ካልሲዎቹን ንጹሕ እና ደረቅ ያድርጉ እና በየ 3 እስከ 6 ወሩ የመጭመቂያ ካልሲዎችን በአዲስ ይተኩ። አዲስ እና የተለየ የህመም ስሜት ከተከሰተ ሐኪም ወዲያውኑ ያነጋግሩ።

የመጭመቂያ ካልሲዎች የቫሪኮስ ቬይን ማስወገድ አይችሉም፣ ግን ተጓዳኝ ህመምን እና እብጠትን ሊቀንሱ ይችላሉ።

የተለመዱ የደም ስር በሽታዎች የትኞቹ  ናቸው?

የተለመዱ የደም ስር በሽታዎች

የተለመዱ የደም ስር በሽታዎች

  • አብዛኛዎቹ የደም ስር በሽታዎች የሚከሰቱት የደም ሥሮች በመዘጋት ወይም የደም ሥሮች ግድግዳ ድክመት ምክንያት ነው። 
  • ዋናው የደም ወሳጅ በሽታ መንስኤ አተሮስክለሮሲስ (በደም ወሳጅ ሥሮች  ውስጥ የስብ ክምችቶች) ነው። አተሮስክለሮሲስ በደም ወሳጅ ግድግዳዎች ውስጥ ቀስ በቀስ በተከማቸ ንጣፎች ምክንያት የደም ስር ውፍረት መጨመሩ አንዳንዴም “ጠንካራ” መሆን ወይም የደም ሥሮች መዘጋት/መጥበብ ችግር ነው።
  • አተሮስክለሮሲስ የደም ወሳጅ ሥሮች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ሊያደርግ ይችላል ወይም ደም ወሳጅ ሥሮች በጊዜ ሂደት የመለጠጥ ችሎታቸውን በማጣት እና ግድግዳቸው በመዳከሙ አኑሪዝም ወደምንለው ደም ወሳጅ ቧንቧ መስፋት ያመጣል። እነዚህ ሁለቱም በደም ወሳጅ ሥሮች ላይ በአተሮስክለሮሲስ የሚደረጉ ለውጦች ከአንዳንድ የአኗኗር ዘይቤዎች እና ከህክምና ምክንያቶች ጋር የተቆራኙ ናቸው። ይህም የደም ስር በሽታን የበለጠ ያጋልጣል።
  • አንዳንድ የተለመዱ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው።

የእግር የደም ወሳጅ ስር በሽታ (Peripheral arterial disease/PAD) ፡-

  • እንደ እግር ባሉ የሰውነት ክፍሎች ደም ወሳጅ  ላይ ለሚከሰት የደም ወሳጅ ቧንቧዎች መዘጋት/መጥበብ በሽታ የተሰጠ ስም ነው። ነገር ግን ይህ በሽታ  እንዳለቦት ከታወቀ፣ አንጎልዎን እና ልብዎን በሚሰጡ የደም ቧንቧዎች ላይ ተመሳሳይ ሂደት ሊከሰት ይችላል። ይህ ለልብ ድካም ወይም ለስትሮክ በሽታ የመጋለጥ እድልዎ ከፍ ያለ ነው።
  • በአተሮስስክሌሮሲስ በሽታ ምክንያት የሚታወክ የደም ስር ከእግር ውጭ በሚሰጡ የደም ወሳጅ ቧንቧዎች ውስጥም ሊከሰት ይችላል። እንደ አንገት ላይ ያለው የካሮቲድ ደም ወሳጅ ቧንቧ አተሮስክለሮሲስ፣ ለስትሮክ መንስኤ ሊሆን ይችላል። በኩላሊት ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ውስጥ የኩላሊት ሽንፈትን ያስከትላል። ወደ አንጀት ደም ወሳጅ ውስጥ ህመምን ያስከትላል ፣ ክብደትን ይቀንሳል ፣ አንጀት ላይ  ከባድ የሆኑ ጉዳቶች ላይ ያስከትላል ። ለሕይወት አስጊ የሆነ አንጀት መሞት እና መበሳት፣ይህም ድንገተኛ  የቀዶ ጥገና ያስከትላል።
  •  
  • የእግር የደም ወሳጅ ስር በሽታ የሚያስከትለው የተለመደው ችግር በእግር ሲራመዱ በእግር ጡንቻዎች ላይ ህመም እና አንዳንዴም የደም ዝውውር በጣም ዝቅተኛ በሚሆንበት ጊዜ በእግር ውስጥ የደም ዝውውር መቀነስ ነው። የ PAD ስርጭት በእድሜ እየጨመረ የሚሄድ እና የልብና የደም ሥር በሽታ ወይም የስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች ከጠቅላላው ህዝብ የበለጠ አደጋ ላይ ናቸው።
  • በእግሮችዎ ላይ መኮማተር ፣ መወጠር ወይም ድክመት ካለብዎ ፣ PAD በመባል የሚታወቀው የደም ስር በሽታ ሊኖርብዎ ይችላል። PAD ወደ እግር መቆረጥ አልፎ ተርፎም የልብ ድካም ወይም ሞት ሊያስከትል ይችላል።  ቀደም ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው!

የአኦርቲክ አኑኢሪዜም:

  • የአኦርቲክ አኑኢሪዝም በሰውነትዎ ውስጥ ትልቁ የደም ስርዎ ግድግዳ ድክመት ነው። የተዳከመውን ክፍልም ወደ መስፋፋት ያመራል እና በመጨረሻም ፍንዳታ ያስከትላሉ።
  • አኑኢሪዝም በጣም ትልቅ ከሆነ ወይም ምልክቶችን የሚያስከትል ከሆነ ለመጠገን ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግዎ ይችላል።  የአኦርቲክ አኑኢሪዜም ጥገና ዓላማ እንደ አኑኢሪዜም ፍንዳታ ወይም ከበድ ያሉ ችግሮችን እንዲሁም በዚህ ምክንያት የሚመጣውን ሞት መከላከል ነው።

ካሮቲድ የደም ቧንቧ አተሮስክሌሮሲስ:

  • የካሮቲድ የደም ስር በሽታ በካሮቲድ ደም ወሳጅ ሥሮች ውስጥ ደምን ወደ አንጎል የሚያቀርበውን ደም ወሳጅ ሥሮች መዘጋት/መጥበብ ያመለክታል። በካሮቲድ ደም ወሳጅ ሥሮች ውስጥ ያለው ንጣፍ ክምችት አደገኛ ነው። ምክንያቱም ወደ አንጎል የደም ፍሰትን ስለሚቀንስ።
  • የካሮቲድ የደም ቧንቧ ቀዶ ጥገና የደም ዝውውርን ያሻሽላል እና እንደ ስትሮክ ወይም ጊዜያዊ ስትሮክ አይነት ጥቃቶችን ያሉ ችግሮች የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል።

ቫሪኮስ / የደም መላሽ ቧንቧዎች መስፋት:

  • ይህ የሚከሰተው የላይኛው ደም መላሽ ሥሮች ሲሰፉ እና መደበኛ ባልሆኑበት ጊዜ ደም ከእግር ወደ ልብ የመላክ ችግር ያጋጥማል። ለዚህ ክስተት በርካታ ምክንያቶች አሉ። በ ላይ ላዩን ያሉ ደም መላሽ ሥሮች ውስጥ ያሉት ቫልቮች አይሰሩም/ ደካማ ሊሆኑ ይችላሉ፣  ወይም የላይኛው ደም መላሽ ሥሮች ከጥልቅ ደም መላሾች ያልተለመደ ከፍተኛ ጫና ሊደርስባቸው ይችላል።
  • በእግር ውስጥ ያለው ደም መላሽ ሥሮች በመደበኛነት መሥራት ካልቻለ ደም ከእግር ወደ ልብ የመላክ ችግር ያጋጥማል እና በእግሮቹ ውስጥ ያለው ግፊት ከፍ ይላል። ይህ በታችኛው እግር ላይ በተለይም በቁርጭምጭሚት አካባቢ ያለውን የደም ዝውውር ይጎዳል ይህም ወደ እብጠት፣ ምቾት ማጣት፣የቆዳ ለውጥ እና በመጨረሻም ወደ ቁስለት ይመራዋል።
  • ሥር የሰደደ የደም መላሽ ሥሮች ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ ይሄዳል። ይሁን እንጂ ሕክምናው በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ከተጀመረ ሊታከም ይችላል። እራስን የመንከባከብ እርምጃዎችን በመውሰድ፣ ህመም እና እብጠት ማቃለል እና በሽታው እንዳይባባስ መከላከል ይችላሉ። በተጨማሪም በሽታውን ለማከም ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግዎ ይችላል።
A Comprehensive Guide to Vascular Services and Treatments in Singapore

የደም ስር ጤና

የደም ስር ጤና ቁልፍ ገጽታዎች እና የደም ስር ጤናን ለመጠበቅ ስለሚወስዷቸው እርምጃዎች ይወቁ!

የዚህ ጽሁፍ አላማ ለታካሚዎቻችን አጠቃላይ ስለ የደም ሥር ጤንነት እና የተለያዩ የደም ሥር በሽታዎች እና ፣ የሕክምና አማራጮችን ማሳወቅ፣ በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያደርጉ ማስተማር፣ እና የደም ሥር ጤንነትዎን እንዲጠብቁ ማበረታታት ነው።

በየዚህ ጽሁፍ የደም ሥር ስርአታችሁን ትልቅ ጠቀሜታ እና በደህንነትዎ ላይ ያለውን ከፍተኛ ተጽእኖ ላሳይ እሞክራለሁ።

የደም ስር  ስርዓት ምንድነው?

  • የደም ስር ስርአታችሁ ደምን በሰውነትዎ ውስጥ በሙሉ ለማጓጓዝ ሃላፊነት ያለው የደም ሥሮች መረብ ነው። የስርአቱ ዋና ክፍሎች ደም ወሳጅ ሥሮች፣ደም መላሽ ሥሮች እና ሊምፋቲክስ ናቸው።
  • ዋናው ተግባሩ ኦክሲጅን እና አስፈላጊ ንጥረ ምግቦችን በደም ወሳጅ ቧንቧዎች ውስጥ ወደ ሁሉም የሰውነት አካላት ማዘዋወር እና ቆሻሻ ምርቶችን እና ካርቦን ዳይኦክሳይድን በደም ቧንቧዎች ውስጥ ማጓጓዝ ነው።

የደም ስር በሽታዎች ምንድን ናቸው?

  • የደም ሥር በሽታ ደም ወሳጅ ሥሮች፣ ደም መላሾች እና የሊምፋቲክ ሥሮችን ያጠቃልላል። ለደም ቧንቧ በሽታ ዋና አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ዋና ዋና ነገሮች፡- አተሮስክለሮሲስ (በደም ወሳጅ ሥሮች  ውስጥ የስብ ክምችቶች)፣ ሲጋራ ማጨስ፣ የስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮል እና የዕድሜ መጨመር ናቸው።
  • የደም ወሳጅ ቧንቧዎች እና ደም መላሽ ሥሮች በሽታ በእግሮች ላይ ለሚከሰቱ ቁስሎች ዋና መንስኤ ሲሆን እግሮች ማጣት ወይም የከፋ በሚሆንበት ጊዜ ሞት ሊያስከትል ይችላል።
  • የደም ሥር ችግሮችን በጊዜ መለየት ወሳኝ ነው። ብዙ የደም ሥር በሽታዎች ከባድ እስኪሆኑ ድረስ ምንም ምልክት አይኖራቸውም። መደበኛ ምርመራዎች ሲያደርጉ ችግሮች ከመባባሳችው በፊት መለየት ይችላሉ።

የቫሪኮስ ደም ሥር

የቫሪኮስ ደም ሥር |Varicose Vein | ምንድን ነው?

  • የቫሪኮስ ደም ሥር ጠመዝማዛ, የተስፋፉ ደም መላሾች ናቸው አብዛኛውን ጊዜ በእግሮቹ ላይ ባሉት ደም መላሾች ላይ ያጋጥማል። ምክንያቱም መቆም እና መራመድ የታችኛው የሰውነት ደም መላሽ ስሮች ላይ ያለውን ጫና ስለሚጨምሩ ነው። የቫሪኮስ ደም ሥር ህመም እና ምቾት ማጣት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ የ  ከባድ ችግሮች ሊያስከትሉ ይችላሉ።

የቫሪኮስ ደም ሥር ምክንያቱ ምንድን ነው?

  • ደም መላሽ ስሮች ደም ከተቀረው የሰውነት ክፍል እንዲሁም እግሮች ወደ ልብ ይመለሳሉ። ደም ወደ ልብ ለመመለስ የታችኛው እግሮች የጡንቻ መኮማተር እንደ ፓምፖች ሆነው ያገለግላሉ። ደም መላሽ ስሮች ያሉ ትናንሽ ቫልቮች የሚከፈቱት ደም ወደ ልብ ሲፈስ ነው፣ ከዚያም ደሙ ወደ ኋላ እንዳይፈስ ይዘጋሉ። እነዚህ ቫልቮች ደካማ ከሆኑ ወይም የተበላሹ ከሆኑ ደም ወደ ኋላ ሊፈስ እና በደም ሥር ውስጥ ሊጠራቀም ይችላል። ይህ በተለይ በሚቆሙበት ጊዜ ደም መላሽ ቧንቧዎች በደም ተሞልተው እንዲቆዩ ያደርጋል። ከዚህ የተነሳ ደም መላሽ ቧንቧዎች እንዲለጠጡ ወይም እንዲስፋፋ ያደርጋል።

የቫሪኮስ ደም ሥር ምልክቶች ምንድን ናቸው ?

የእግር ህመም ወይም የክብደት ስሜት

ለረጅም ጊዜ ከተቀመጡ ወይም ከቆሙ በኋላ የሚባባስ ህመም

ማቃጠል፣ ማሳከክ

የታችኛው እግሮች እብጠት

የቆዳ ቀለም ለውጦች

የቫሪኮስ ደም ሥር የሚያጋልጡ ምክንያቶች ምንድን ናቸው ?

የዕድሜ መጨመር / እርጅና

በሌሎች የቤተሰብ አባላት የበሽታው መኖር

ሴቶች በሽታውን የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው (ከሆርሞን መጠን ለውጦች ጋር የተያያዘ ነው)

እርግዝና

ቀደም ሲል የደም መርጋት ታሪክ ካለ

ከመጠን ያለፈ ውፍረት

ረጅም ጊዜ መቆም ወይም መቀመጥ የሚጠይቅ ሥራ

ረጅም ቁመት

የቫሪኮስ ደም ሥር የሚያስከትለው መዘዝ ምንድን ነው?

የእግር ህመም እና እብጠት

በቆዳ ቀለም ላይ ለውጦች (ብዙውን ጊዜ ቁስለት ከመፈጠሩ በፊት ይጀምራል)

በቁርጭምጭሚት አካባቢ የሚያሰቃዩ ቁስሎች

የደም መርጋት

የደም መፍሰስ (አልፎ አልፎ ከቆዳው አጠገብ ያሉ የደም ስሮች ይፈነዳሉ)

የቫሪኮስ ደም ሥር እንዴት መከላከል ይቻላል?

ከፍ ያለ ተረከዝ ጫማ ማስወገድ

ጥብቅ ልብሶችን ያስወግዱ

ጤናማ ክብደትን መጠበቅ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

ለረጅም ጊዜ ከመቆም ወይም ከመቀመጥ ይቆጠቡ

ሲቀመጡ ወይም ሲተኙ እግሮችዎን ከፍ ማድረግ

እንዴት ሊታከም ይችላል?

የቫሪኮስ ደም ሥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ ይሄዳል። ይሁን እንጂ ሕክምናው በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ከተጀመረ ሊታከም ይችላል። እራስን የመንከባከብ እርምጃዎችን,  እና በሽታው እንዳይባባስ መከላከል ይችላሉ.

ለቫሪኮስ ደም ሥር የሚደረግ ሕክምና ራስን የመንከባከብ እርምጃዎችን በመውሰድ፣ የጨመቅ ስቶኪንጎችን በመጠቀም ስሜቶቹን ማቃለል እና በሽታው እንዳይባባስ መከላከል ይችላሉ። በተጨማሪም ራስን የመንከባከብ እርምጃዎች እና የመጭመቂያ ስቶኪንጎች የማይሰሩ ከሆነ በሽታውን ለማከም ቀዶ ጥገናዎችን ወይም ሌሎች የሕክምና ሂደቶች  ሊያካትት ይችላል።

የቫሪኮስ ደም ሥር የማከም ጥቅሞች

  • የተሻሻለ የእግሮች ገጽታ
    • ህመምን ይቀንሳል እና ምቾትን ያሻሽላል
    • የእግሮች የደም ዝውውርን ያሻሽላል
    • የደም መርጋት አደጋን ይቀንሳል
    • እንቅስቃሴን በእጅጉ ያሻሽላል