የተለመዱ የደም ስር በሽታዎች የትኞቹ  ናቸው?

የተለመዱ የደም ስር በሽታዎች

የተለመዱ የደም ስር በሽታዎች

  • አብዛኛዎቹ የደም ስር በሽታዎች የሚከሰቱት የደም ሥሮች በመዘጋት ወይም የደም ሥሮች ግድግዳ ድክመት ምክንያት ነው። 
  • ዋናው የደም ወሳጅ በሽታ መንስኤ አተሮስክለሮሲስ (በደም ወሳጅ ሥሮች  ውስጥ የስብ ክምችቶች) ነው። አተሮስክለሮሲስ በደም ወሳጅ ግድግዳዎች ውስጥ ቀስ በቀስ በተከማቸ ንጣፎች ምክንያት የደም ስር ውፍረት መጨመሩ አንዳንዴም “ጠንካራ” መሆን ወይም የደም ሥሮች መዘጋት/መጥበብ ችግር ነው።
  • አተሮስክለሮሲስ የደም ወሳጅ ሥሮች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ሊያደርግ ይችላል ወይም ደም ወሳጅ ሥሮች በጊዜ ሂደት የመለጠጥ ችሎታቸውን በማጣት እና ግድግዳቸው በመዳከሙ አኑሪዝም ወደምንለው ደም ወሳጅ ቧንቧ መስፋት ያመጣል። እነዚህ ሁለቱም በደም ወሳጅ ሥሮች ላይ በአተሮስክለሮሲስ የሚደረጉ ለውጦች ከአንዳንድ የአኗኗር ዘይቤዎች እና ከህክምና ምክንያቶች ጋር የተቆራኙ ናቸው። ይህም የደም ስር በሽታን የበለጠ ያጋልጣል።
  • አንዳንድ የተለመዱ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው።

የእግር የደም ወሳጅ ስር በሽታ (Peripheral arterial disease/PAD) ፡-

  • እንደ እግር ባሉ የሰውነት ክፍሎች ደም ወሳጅ  ላይ ለሚከሰት የደም ወሳጅ ቧንቧዎች መዘጋት/መጥበብ በሽታ የተሰጠ ስም ነው። ነገር ግን ይህ በሽታ  እንዳለቦት ከታወቀ፣ አንጎልዎን እና ልብዎን በሚሰጡ የደም ቧንቧዎች ላይ ተመሳሳይ ሂደት ሊከሰት ይችላል። ይህ ለልብ ድካም ወይም ለስትሮክ በሽታ የመጋለጥ እድልዎ ከፍ ያለ ነው።
  • በአተሮስስክሌሮሲስ በሽታ ምክንያት የሚታወክ የደም ስር ከእግር ውጭ በሚሰጡ የደም ወሳጅ ቧንቧዎች ውስጥም ሊከሰት ይችላል። እንደ አንገት ላይ ያለው የካሮቲድ ደም ወሳጅ ቧንቧ አተሮስክለሮሲስ፣ ለስትሮክ መንስኤ ሊሆን ይችላል። በኩላሊት ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ውስጥ የኩላሊት ሽንፈትን ያስከትላል። ወደ አንጀት ደም ወሳጅ ውስጥ ህመምን ያስከትላል ፣ ክብደትን ይቀንሳል ፣ አንጀት ላይ  ከባድ የሆኑ ጉዳቶች ላይ ያስከትላል ። ለሕይወት አስጊ የሆነ አንጀት መሞት እና መበሳት፣ይህም ድንገተኛ  የቀዶ ጥገና ያስከትላል።
  •  
  • የእግር የደም ወሳጅ ስር በሽታ የሚያስከትለው የተለመደው ችግር በእግር ሲራመዱ በእግር ጡንቻዎች ላይ ህመም እና አንዳንዴም የደም ዝውውር በጣም ዝቅተኛ በሚሆንበት ጊዜ በእግር ውስጥ የደም ዝውውር መቀነስ ነው። የ PAD ስርጭት በእድሜ እየጨመረ የሚሄድ እና የልብና የደም ሥር በሽታ ወይም የስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች ከጠቅላላው ህዝብ የበለጠ አደጋ ላይ ናቸው።
  • በእግሮችዎ ላይ መኮማተር ፣ መወጠር ወይም ድክመት ካለብዎ ፣ PAD በመባል የሚታወቀው የደም ስር በሽታ ሊኖርብዎ ይችላል። PAD ወደ እግር መቆረጥ አልፎ ተርፎም የልብ ድካም ወይም ሞት ሊያስከትል ይችላል።  ቀደም ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው!

የአኦርቲክ አኑኢሪዜም:

  • የአኦርቲክ አኑኢሪዝም በሰውነትዎ ውስጥ ትልቁ የደም ስርዎ ግድግዳ ድክመት ነው። የተዳከመውን ክፍልም ወደ መስፋፋት ያመራል እና በመጨረሻም ፍንዳታ ያስከትላሉ።
  • አኑኢሪዝም በጣም ትልቅ ከሆነ ወይም ምልክቶችን የሚያስከትል ከሆነ ለመጠገን ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግዎ ይችላል።  የአኦርቲክ አኑኢሪዜም ጥገና ዓላማ እንደ አኑኢሪዜም ፍንዳታ ወይም ከበድ ያሉ ችግሮችን እንዲሁም በዚህ ምክንያት የሚመጣውን ሞት መከላከል ነው።

ካሮቲድ የደም ቧንቧ አተሮስክሌሮሲስ:

  • የካሮቲድ የደም ስር በሽታ በካሮቲድ ደም ወሳጅ ሥሮች ውስጥ ደምን ወደ አንጎል የሚያቀርበውን ደም ወሳጅ ሥሮች መዘጋት/መጥበብ ያመለክታል። በካሮቲድ ደም ወሳጅ ሥሮች ውስጥ ያለው ንጣፍ ክምችት አደገኛ ነው። ምክንያቱም ወደ አንጎል የደም ፍሰትን ስለሚቀንስ።
  • የካሮቲድ የደም ቧንቧ ቀዶ ጥገና የደም ዝውውርን ያሻሽላል እና እንደ ስትሮክ ወይም ጊዜያዊ ስትሮክ አይነት ጥቃቶችን ያሉ ችግሮች የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል።

ቫሪኮስ / የደም መላሽ ቧንቧዎች መስፋት:

  • ይህ የሚከሰተው የላይኛው ደም መላሽ ሥሮች ሲሰፉ እና መደበኛ ባልሆኑበት ጊዜ ደም ከእግር ወደ ልብ የመላክ ችግር ያጋጥማል። ለዚህ ክስተት በርካታ ምክንያቶች አሉ። በ ላይ ላዩን ያሉ ደም መላሽ ሥሮች ውስጥ ያሉት ቫልቮች አይሰሩም/ ደካማ ሊሆኑ ይችላሉ፣  ወይም የላይኛው ደም መላሽ ሥሮች ከጥልቅ ደም መላሾች ያልተለመደ ከፍተኛ ጫና ሊደርስባቸው ይችላል።
  • በእግር ውስጥ ያለው ደም መላሽ ሥሮች በመደበኛነት መሥራት ካልቻለ ደም ከእግር ወደ ልብ የመላክ ችግር ያጋጥማል እና በእግሮቹ ውስጥ ያለው ግፊት ከፍ ይላል። ይህ በታችኛው እግር ላይ በተለይም በቁርጭምጭሚት አካባቢ ያለውን የደም ዝውውር ይጎዳል ይህም ወደ እብጠት፣ ምቾት ማጣት፣የቆዳ ለውጥ እና በመጨረሻም ወደ ቁስለት ይመራዋል።
  • ሥር የሰደደ የደም መላሽ ሥሮች ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ ይሄዳል። ይሁን እንጂ ሕክምናው በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ከተጀመረ ሊታከም ይችላል። እራስን የመንከባከብ እርምጃዎችን በመውሰድ፣ ህመም እና እብጠት ማቃለል እና በሽታው እንዳይባባስ መከላከል ይችላሉ። በተጨማሪም በሽታውን ለማከም ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግዎ ይችላል።
A Comprehensive Guide to Vascular Services and Treatments in Singapore
0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *